Atoms, the smallest particles of matter that retain the properties of the matter, are made of protons, electrons, and neutrons. |
አተሞች፣ የቁሱ ባህሪያት ይዘው የሚቀሩ ከሁሉም የሚያንሱት የቁስ እኑሶች ከፕሮቶኖች፣ ኤሌክትሮኖች እና ኒውትሮኖች የተሰሩ ናቸው። |
Protons have a positive charge, Electrons have a negative charge that cancels the proton's positive charge. |
ፕሮቶኖች አዎንታዊ ሙል አላቸው፣ ኤሌክትሮኖች ደግሞ የፕሮቶኖች አዎንታዊ ሙልን የሚያጠፋ አሉታዊ ሙል አላቸው። |
Neutrons are particles that are similar to a proton but have a neutral charge. |
ኒውትሮኖች ወገን የለሽ ሙል ያላቸው እንደ ፕሮቶኖች የሚመሳሰሉ እኑሶች ናቸው። |
There are no differences between positive and negative charges except that particles with the same charge repel each other and particles with opposite charges attract each other. |
በአዎንታዊ እና አሉታዊ ሙሎች መካከል ምንም አይነት ልዩነት የለም ነገር ግን ተመሳሳይ ሙል ያላቸው እኑሶች እርስ በእርስ ይባረራሉ ደግሞም ተቃራኒ ሙል ያላቸው እኑሶች እርስ በእርስ ይሳሳባሉ። |
If a solitary positive proton and negative electron are placed near each other they will come together to form a hydrogen atom. |
ብቸኛ አዎንታዊ ፕሮቶን እና አሉታዊ ኤሌክትሮን ተቀራርበው ካስቀመጥናቸው አንድ ላይ ይሁኦኑና የሃይድሮጂን አቶም ይፈጥራሉ። |
This repulsion and attraction (force between stationary charged particles) is known as the Electrostatic Force and extends theoretically to infinity, but is diluted as the distance between particles increases. |
ይህ ግፍትረት እና ስበት (በሁለት ጉልታዊ ባለሙል እኑሶች መካከል የሚገኝ ሃይል) የኤሌትሮስታቲካዊ ሃይል በመባል ይታወቃል ደግሞም በቲዎሪ እስከ እልቆቢስ ይዘረጋል፤ ነገር ግን በእኑሶቹ መካከል ያለው ርቀት በጨመረ ቁጥር ይደበዝዛል። |
When an atom has one or more missing electrons it is left with a positive charge, and when an atom has at least one extra electron it has a negative charge. |
አቶም አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሚጎድሉ ኤሌክትሮኖች ሲኖሩት አዎንታዊ ሙል ይኖረዋል፣ ደግሞም አቶም ቢያንስ አንድ ተጨማሪ ኤሌክትሮን ሲኖረው አሉታዊ ሙል ይኖረዋል። |
Having a positive or a negative charge makes an atom an ion. |
አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ሙል መኖሩ አቶምን አየን ያደርገዋል። |
Atoms only gain and lose protons and neutrons through fusion, fission, and radioactive decay. |
አተሞች ፕሮቶኖችን እና ኒውትሮኖችን የሚያገኙት እና የሚያጡት በእርስሰት፣ በብትነት እና በራዲዮአክቲቫዊ ብስብሰት ነው። |
Although atoms are made of many particles and objects are made of many atoms, they behave similarly to charged particles in terms of how they repel and attract. |
ምንም እንኳን አተሞች ከብዙ እኑሶች የተሠሩ ቢሆኑና ነገሮች ደግሞ ከብዙ አተሞች የተሠሩ ቢሆኑም ከመገፋፋት እና ከመሳሳብ ረገድ ሲታዩ ከባለሙል እኑሶች ጋር ተመሳሳይ ባህሪ አላቸው። |
In an atom the protons and neutrons combine to form a tightly bound nucleus. |
በአቶም ውስጥ ፕሮቶኖች እና ኒውትሮኖች ተጣምረው ጥብቅ የሆነ ኒውክሊየስ ይፈጥራሉ። |
This nucleus is surrounded by a vast cloud of electrons circling it at a distance but held near the protons by electromagnetic attraction (the electrostatic force discussed earlier). |
ይህ ኒውክሊየስ በርቀት በሚዞሩት እጅግ በጣም ብዙ በሆነ የኤሌክትሮኖች ደመና የተከበበ ነው ደግሞም በኤሌትሮመግነጢሳዊ ስበት ከፕሮቶኖች አቅራቢያ ተይዟል (ቀደም ሲል የተብራራው ኤሌትሮስታቲካዊ ሃይል)። |
The cloud exists as a series of overlapping shells / bands in which the inner valence bands are filled with electrons and are tightly bound to the atom. |
ደመናው እንደ ተከታታይና ተደራራቢ ቀፎዎች/ጥብጣቦች ሲሆን በውስጡም ያለው የውስጠኛው ቫለንስ ጥብጣቦች በኤሌክትሮኖች የተሞሉ እና ከአቶሙ ጋር በጥብቅ የተሳሰሩ ናቸው። |
The outer conduction bands contain no electrons except those that have accelerated to the conduction bands by gaining energy. |
ጉልበትን በማግኘት ወደ ውጭ አስተላልፎሽ ጥብጣቦች ሸምጥጠው ከሄዱ በስተቀር የውጭ አስተላልፎሽ ጥብጣቦች ምንም ኤሌክትሮኖች የላቸውም። |
With enough energy an electron will escape an atom (compare with the escape velocity of a space rocket). |
በቂ ጉልበት ካገኘ ኤሌክትሮን ከአቶም ያመልጣል (ከጠፈር ሮኬት የምልጠት ፍጥነት ጋር አነጻጽሩ)። |
When an electron in the conduction band decelerates and falls to another conduction band or the valence band a photon is emitted. |
በኮንዳክሽን ባንድ ውስጥ ያለ ኤሌክትሮን ሽምጠጣውን ሲቀንስና ወደ ሌላ የአስተላልፎሽ ጥብጣብ ወይንም ወደ ቫሌንስ ጥብጣብ ሲወድቅ ፎቶን ይፈልቃል። |
This is known as the photoelectric effect. |
ይህም ፎቶሌትሪካዊ ፍትን በመባል ይታወቃል። |