The definition of health has evolved over time. |
ለጤና የሚሰጠው ትርጉም እያዘገመ ከጊዜ አክዋያ ተለውጥዋል። |
In keeping with the biomedical perspective, early definitions of health focused on the theme of the body's ability to function; health was seen as a state of normal function that could be disrupted from time to time by disease. |
የባዮሜዲካል እይታ እንደሚያስገነዝበው የጤና ቀደምተ ፍቺዎች ያተኩሩ የነበረው ሰለ ሰው አካል ብቁነት፣ ጤና ማለት በተለምዶ ብቁ የሆነ እንቅስቃሴ ሆኖ በበሽታ ምክንያት ግን አልፎ አልፎ የሚስተግዋጎል ነበር። |
An example of such a definition of health is: "a state characterized by anatomic, physiologic, and psychological integrity; ability to perform personally valued family, work, and community roles; ability to deal with physical, biologic, psychological, and social stress". |
ይህንን መሰል የጤና ትርግዋሜ የያዘ ምሳሌ፡ "እሙን የሆነ የሰውነት ክፍስ፣ አካል እና ስነልቦና፤ የቤተሰብን እሴት፣ ስራና ማህበረሰብን በብቃት የሚያከናወን፤ አካላዊ፣ ህያዊ፣ ስነልቦናዊ እና ማህበራዊ ጭንቀትን በብቃት የሚወጣ"። |
Then, in 1948, in a radical departure from previous definitions, the World Health Organization (WHO) proposed a definition that aimed higher, linking health to well-being, in terms of "physical, mental, and social well-being, and not merely the absence of disease and infirmity". |
ከዛም፣ በፈ.አ. 1948 የአለም ጤና ድርጅት ቀድሞ የነበረውን እሩቅ ጥሎ ከፍ ያለ ማለትም ጤናን ከሁለመናዊ ድህንነት ያዛመደ የትርጉም ሃሳብ በዚህ መልክ አቀረበ "አካላዊ፣ አእምሮአዊ እንዲሁም ማሀበራዊ ደህንነትን ያካተተና በበሽታና በድክመት በቻ ያልተወሰነ"። |
Although this definition was welcomed by some as being innovative, it was also criticized as being vague, excessively broad, and was not construed as measurable. |
ይህን ፍቺ እንደ አዲስ ግኝት አድርገው የነበሩ ቢሆንም በሌሎች ደግሞ ግልጽ ያልሆነ፣ ያለመጠን የሰፋ፣ ልኩ ሊታወቅ የማይችል ትርግዋሜ ተብሎ ተተችትዋል። |
For a long time it was set aside as an impractical ideal and most discussions of health returned to the practicality of the biomedical model. |
ለረጅም ጊዜ ሊተገበር የማይችል ሃሳብ ተብሎ ቢገለልም ጤና ዙሪያ የሚደረጉ ውይይቶች መለስ ብለው ወደ ባዮሜዲካል ሞዴል ተግባራዊነት ተመልሰዋል። |
Just as there was a shift from viewing disease as a state to thinking of it as a process, the same shift happened in definitions of health. |
አንድ በሽታ እንደ ሁኔታ ከዚያም እንደ ሂደት ለመታየት እንደበቃው ሁሉ የጤና ፍቺም እንዲሁ ለውጥ አሳየ። |
Again, the WHO played a leading role when it fostered the development of the health promotion movement in the 1980s. |
የአለምጤና ድርጅት በድጋሚ በፈ.አ. በ1980ዎቹ መሪ ሚና በመጫወት የጤና ልማትን እንቅስቃሴ በመደገፍ የማስተዋወቂያ ዘመቻ አካሂድዋል። |
This brought in a new conception of health, not as a state, but in dynamic terms of resiliency, in other words, as "a resource for living". |
ይህም ጤናን እንደ አንድ ሁኔታ ሳይሆን ተለዋዋጭ የመቋቋም በቃት ያለው በሌላ አነጋገር "የህይወት ምንጭ" መሆኑን በአዲስ መልኩ ተጸነሰ። |
The 1984 WHO revised definition of health defined it as "the extent to which an individual or group is able to realize aspirations and satisfy needs, and to change or cope with the environment. Health is a resource for everyday life, not the objective of living; it is a positive concept, emphasizing social and personal resources, as well as physical capacities". |
በፈ.አ. 1984 የአለም ጤና ድርጅት የሰጠውን ትርግዋሜ በአዲስ ፍች ከልሶ "አንድ ግለሰብ ወይንም የሰው ስብስብ የተመኘውን ከግብ አድርሶ ፍላጎቱን ማሟላት፣ እራስን መለወጥ እና አካባቢውን መቋቋም ሲችል። ጤና የእለት ህይወት የሃብት ምንጭ እንጂ የኑሮ ዋና አላማ አይደለችም፤ አዎንታዊ ጽንሰ ሃሳብ፣ የማህበራዊና የግል ሃብት፣ እንዲሁም የአካል ብቃቶች ናት"። |
Thus, health referred to the ability to maintain homeostasis and recover from insults. |
ስለዚህም ጤና የሚያስመለክተው ከስድም ተርፎ የተመቻቸ ተግባር ወይንም ሆምዮስታስሲን ነው። |
Mental, intellectual, emotional, and social health referred to a person's ability to handle stress, to acquire skills, to maintain relationships, all of which form resources for resiliency and independent living |
ባጠቃላይ ጭንቀትን የመቋቋም ብቃት፣ ክህሎት የማዳበር አቅም፣ ግንኙነቶችን መጠበቅ፣ እራስን ችሎና ትቋቁሞ ለመኖር የሚያስፈልጉ ሃብቶች የሚገኙት ከአእምሮአዊ፣ ምሁራዊ፣ ስሜታዊ እና ማህበራዊ ጤንነት ነው። |