Public health has been described as "the science and art of preventing disease, prolonging life and promoting health through the organized efforts and informed choices of society, organizations, public and private, communities and individuals." |
የሕብረተሰብ ጤና "በሽታን የመከላከል፣ ህይወትን የማራዘም እና ጤናን በተቀናጀ እና በመረጃ በተደገፈ ማህበራዊ፣ ድርጅታዊ፣ ማሕበረሰባዊ እና ግላዊ ጥረት የመጠበቅ ሳይንስ እና ጥበብ" በመባል ተገልጿል። |
It is concerned with threats to the overall health of a community based on population health analysis. |
ለማህበረሰብ ሁለንተናዊ ጤና ጠንቅ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች በሕዝብ ጤና ትንተና ላይ በመመስረት ያተኩራል።
|
The population in question can be as small as a handful of people or as large as all the inhabitants of several continents (for instance, in the case of a pandemic). |
ትኩረት የሚደረግበት ህዝብ በጣት ከሚቆጠር ሕዝብ ጀምሮ የብዙ አህጉራት ጠቅላላ ነዋሪዎችን ሊያጠቃልል ይችላል (ለምሳሌ፣ እንደ ወረርሽኝ)። |
Public health has many sub-fields, but typically includes the interdisciplinary categories of epidemiology, biostatistics and health services. |
የሕብረተሰብ ጤና ብዙ ክፍለ-ዘርፎች አሉት፣ በአብዛኛው ግን እነዚህን ተጓዳኝ ዘርፎች ኤፒደሚዮሎጂ፤ ባዮስታትቲክስ እና የጤና አገልግሎቶችን ይይዛል። |
Environmental health, community health, behavioral health, and occupational health are also important areas of public health. |
የአካባቢ ጤና፣ የማህበረሰብ ጤና፣ የባህሪ ጤና እና የሙያ ጤና ሌሎች አስፈላጊ የሕብረተሰብ ጤና ዘርፎች ናቸው። |
The focus of public health interventions is to prevent and manage diseases, injuries and other health conditions through surveillance of cases and the promotion of healthy behavior, communities, and (in aspects relevant to human health) environments. |
የሕብረተሰብ ጤና ሙያዊ ትኩረት በሽታን፣ ጉዳታቾን እና ሌሎች የጤና እክሎችን |
Its aim is to prevent health problems from happening or re-occurring by implementing educational programs, developing policies, administering services and conducting research. |
አላማው የጤና እክሎች ከመነሻው ወይም ዳግም እንዳይከሰቱ በትምህርት መርሃግብር፣ ፖሊሲዎችን በማበልጽግ፣ አገልግሎቶችን በማቅረብ እና ጥናቶችን በማካሄድ መከላከል ነው። |
In many cases, treating a disease or controlling a pathogen can be vital to preventing it in others, such as during an outbreak. |
በአብዛኛው ጊዜ በሽታን ማከም ወይም በሽታ አምጪ ተህዋስያንን መቆጣጠር በሌሎች ላይ እንዳይከሰት ወሳኝ ነው፣ ለምሳሌ በወረርሽኝ ወቅት። |
Vaccination programs and distribution of condoms to prevent the spread of communicable diseases are examples of common preventive public health measures, as are educational campaigns to promote vaccination and the use of condoms (including overcoming resistance to such). |
የክትባት መርሃ ግብሮች እና ኮንደም ማከፋፈል ተላላፊ በሽታዎችን ለመግታት ከሚወሰዱ የሕብረተሰብ ጤና እርምጃዎች ውስጥ የተለመዱ ምሳሌዎች ናቸው፣ እንዲሁም የክትባት እውቀትን እና የኮንዶም አጠቃቀምን የሚያሳድጉ የትምህርት ዘመቻዎች ከምሳሌ ውስጥ ይመደባሉ (ይህንን የሚቃወሙ ሃሳቦችን ማሸነፍን ይጨምራል)። |