Unicode is an industry standard whose goal is to provide the means by which text of all forms and languages can be encoded for use by computers through a single character set. |
ዩኒኮድ ዓላማው በአንዲት የቁምፊ ስብስብ አማካኝነት የሁሉም አይነቶች እና ቋንቋዎች ጽሑፍ በኮምፒውተር ውስጥ ስራ ላይ መዋል የሚችሉበት መንገድ ማቅረብ የሆነ የኢንዱስትሪ ደረጃ መስፈርት ነው። |
Originally, text-characters were represented in computers using byte-wide data: each printable character (and many non-printing, or "control" characters) were implemented using a single byte each, which allowed for 256 characters total. |
መጀመሪያ ላይ የጽሑፍ ቁምፊዎች በኮምፒውተሮች ውስጥ የሚወከሉት የባይት ስፋት ባለው ውሂብ ነበር፦ እያንዳንዱ ሊታተም የሚችል ቁምፊ (እና ብዙ የማይታተሙ ወይም «የመቆጣጠሪያ» ቁምፊዎች) የሚተገበሩት ለእያንዳንዱ አንድ ባይት በመጠቀም ነበር፣ ይህም በጠቅላላ 256 ቁምፊዎችን ነው የሚፈቅደው። |
However, globalization has created a need for computers to be able to accommodate many different alphabets (and other writing systems) from around the world in an interchangeable way. |
ይሁንና፣ የሉላዊነት መምጣት ኮምፒውተሮች በመላው ዓለም ያሉ ብዙ የተለያዩ ፊደላትን (እና ሌሎች የጽሕፈት ስርዓቶችን) ተለዋዋጭ በሆነ መልኩ ማስተናገድ መቻል አስፈላጊ አድርጓል። |
The old encodings in use included ASCII or EBCDIC, but it was apparent that they were not capable of handling all the different characters and alphabets from around the world. |
ስራ ላይ የነበሩ የድሮ ቅየራዎች ASCII እና EBCDIC ያካትታሉ፣ ነገር ግን በመላው ዓለም ያሉ ሁሉም የተለያዩ ቁምፊዎችን እና ፊደላትን የማስተናገድ አቅም እንደሌላቸው ግልጽ ሆነ። |
The solution to this problem was to create a set of "wide" 16-bit characters that would theoretically be able to accommodate most international language characters. |
ለዚህ ችግር የተሰጠው መፍትሔ በጽንሰ-ሐሳብ ደረጃ አብዛኛዎቹን የአለምአቀፍ ቋንቋ ቁምፊዎች ማስተናገድ የሚችል «ሰፊ» የሆነ ባለ16-ቢት ቁምፊዎች ስብስብ መፍጠር ነበር። |
This new charset was first known as the Universal Character Set (UCS), and later standardized as Unicode. |
ይህ አዲስ የቁምፊ ስብስብ መጀመሪያ ሁለገብ የቁምፊ ስብስብ (Universal Character Set, UCS) ተብሎ ይታወቅ ነበር፣ በኋላ ላይ ዩኒኮድ (Unicode) ተብሎ ተሰየመ። |
However, after the first versions of the Unicode standard it became clear that 65,535 (216) characters would still not be enough to represent every character from all scripts in existence, so the standard was amended to add sixteen supplementary planes of 65,536 characters each, thus bringing the total number of representable code points to 1,114,112. |
ይሁንና፣ ከመጀመሪያዎቹ የዩኒኮድ መስፈርት ስሪቶች በኋላ 65,535 (216) ቁምፊዎች አሁንም እስካሁን ድረስ የተፈጠረ የእያንዳንዱ ጽሕፈት ቁምፊ ለመወከል በቂ እንደማይሆን ግልጽ ሆነ፣ ስለዚህ የመስፈርት ደረጃው እያንዳንዳቸው 65,535 ቁምፊዎች የያዙ 16 ተጨማሪ የማሟያ መደቦችን እንዲያክል ተስተካከለ፣ በዚህም ሊወከሉ የሚችሉ ጠቅላላ የኮድ ነጥቦች ብዛት ወደ 1,114,112 አድርሶታል። |
To this date, less than 10% of that space is in use. |
እስካ ሁን ድረስ ከዚያ መጠን ውስጥ ከ10% ያነሰ ነው ጥቅም ላይ የዋለው። |