When preparing your advertisement, you should first define your product's Unique Selling Proposition (USP). |
ማስታወቂያህን ስታዘጋጅ በመጀመርያ ምርትህን በልዩ ሁኔታ ሊያሸጥልህ የሚችል ነጥብ አስቀድመህ ልታዘጋጅ ይገባል። |
To find the USP, ask yourself "How is this product different?" |
በልዩ ሁኔታ ምርትህን ሊያሸጥልህ የሚችል ነጥብ ለማግኘት መጀመርያ ራስህን "ይህ ምርት እንዴት ልዩ ሆነ?" ብለህ ጠይቅ። |
Make a list of your product's pros and cons. |
የምርትህን በጎ ገፅታንና መጥፎ ገፅታን በዝርዝር አስቀምጥ። |
This will help you think about what message you want your ad to send. |
ይሄ በማስታወቅያህ ላይ ምን ዓይነት መልዕክት ለማስተላለፍ እንደፈለግክ እንድታስበብት ያደርግሃል። |
Positioning is an attempt to place a product into a certain category in consumers' minds: "the best", for example (best deodorant, best soda, etc.) ("The best" is, however, extremely difficult to establish for a new brand). |
መደብ መስጠት የምርትህን ዓይነት በደንበኞች አዕምሮ ተቀርፆ እንዲቀር ያደርገዋል። ለምሳሌ "ምርጥ ዲዮድራንት" ወይንም "ምርጥ ለስላሳ መጠጥ።" (አዲስ ምርት ከሆነ ግን "ምርጥ" የሚለውን መለያ ለመጠቀም አዳጋች ያደርገዋል።) |
Types of positioning are Against (eg, Hertz vs. Avis, 7-up vs. colas), Niche (a sub-division of a category), New, and Traditional. |
የመደብ ዓይነቶችን ስናይ፣ ለምሳሌ ኸርዝ ከአቪስ ጋር፣ ሰቨን አፕ ከ ኮላ ጋር እያልን ማየት እንችላለን። ክፍልፋይ መደቦች ደግሞ ለምሳሌ አዲስ ወይ አሮጌ እንደ ማለት ነው። |
A Brand Character Statement sets the tone for an entire campaign. |
ልዩ የምርት ዓይነት መገለጫ የማስታወቂያውን ዘመቻ ድምፀት የመወሰን ኃይል አለው። |
A simple way to start preparing your advertisement is with this statement: "Advertising will ____A_____ ____B_____ that ____C_____ is ____D_____. Support will be ____E_____. Tone will be ____F_____." where A is a verb, B is a target demographic (such as, "girls between 14-18 years old"), C is your product, D is an adjective or phrase. |
የማስታወቂያ ዘመቻህን ለመጀመር ቀላሉ መንገድ በሚቀጥለው ዓረፍተ ነገር መጀመር ነው። ማስታወቂያው __ሀ__ ሲሆን የሚመለከተው __ለ__ __ሐ__ን ማቅረብ __መ__። የሽያጭ እገዛ __ሠ__ ሲሆን የማስታወቂያው ድምፀት ደግሞ __ረ__ ይሆናል። በዚህ የማስታወቂያ ስሌት መሰረት "ሀ" ግስ "ለ" ማስታወቂያው የሚመለከታቸው የማሕበረሰብ ክፍሎች (ለምሳሌ ዕድሜያቸው ከ14 ፡ 15 የሆኑ ሴቶች)፣ "ሐ" ደግሞ ምርት እንዲሁም "መ" ገላጭ ቃል ተደርጎ ይወሰዳል። |
E is what the meat of your ad will be. |
"ሠ" የማስታወቂያህ ጮማ ቃል ነው። |
F is your ad's "attitude". |
"ረ" ደግሞ ያንተ ማስታወቂያውን የምታይበት አመለካከትህ ነው። |
For example, "Advertising will convince artistic types age 18-35 that Apple computers are hip and cool. Support will be two men discussing Macs and PCs. Tone will be humorous." |
ለምሳሌ "ማስታወቂያው ዕድሜያቸው ከ18 ፡ 35 የሆኑ የማሕበረሰብ ክፍል ኣባላት ላይ ያተኮረ ሲሆን ዋና መልዕክቱም የአፕል ኮምፒውተሮች በጣም ተወዳጅና ምርጥ እንደሆኑ ማሳየት ነው። ማሳያ የሚሆነው የአፕልና የዊንዶውስ ተጠቃሚ የሆኑ ሁለት ግለሰቦች የሚያደርጉት ውይይት ሲሆን ውይይቱም አስቂኝና አዝናኝ ይሆናል።" |
Part B of this strategy statement is the target audience. |
የእቅዱ ሁለተኛው አካል ማስታወቂያው የሚመለከተው አካል ነው። |
Advertisers use many methods to gain information about this group, including demographics, psychographics (how the target thinks), and focus groups. |
ማስታወቂያ ነጋሪዎች ማስታወቂያው ስለሚመለከተው ክፍል ማሐበረሰባዊ እሴትን የ አመለካከት ሂደትን የመሳሰሉ የተለያዩ ጥናቶችን ለማድረግ ብዙ መንገዶችን ሊጠቀሙ ይችላሉ። |
Part C is the product itself. |
ክፍል ሶስት ራሱ ምርቱ ነው። |
Advertisers spend time studying this as well. |
ማስታወቂያ ነጋሪዎች በዚህም ላይ ጥናት ለማካሄድ ጊዜያቸውን ይሰዋሉ። |
Important questions to ask are "Why would anybody buy this?" "What's the product's advantage?" and "What is the client's image?" |
በዚህ ቅፅበት መጠየቅ የሚገባቸው ጥያቄዎች "ሰዉ ይህን ምርት ለምን ይገዛል?"፣ "የዚህ ምርት ጠቀሜታው ምንድን ነው?"፣ "የደንበኛው ገፅታስ ምን ዓይነት ነው?" የሚሉ ናቸው። |
The last one is important to consider in order to make sure that your ad doesn't jar with the public perception the company has created for itself. |
የመጨረሻው ጠቃሚው ነጥብ ሕዝቡ ስለ ድርጅቱ ያለው አመለካከት በማስታወቂያው የተነሳ እንዳይበረዝ መጠንቀቅ እንዳለብን ነው። |
For example, hip or edgy ads probably won't go over well with a company that has a public image of being "conservative" and/or "family friendly." |
ለምሳሌ መረን የለቀቁ ማስታወቂያዎች ከዚህ በፊት ወግ አጥባቂ በሆኑ ማስታወቂያዎቹ ለሚታወቅ የቤተሰብ ምርጫ ለሆነ ድርጅት ጋር አብረው አይሄዱም። |